ማስታወቂያ
*****
ለፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ3ተኛ ዙር የንግድ/ድርጅት ቤቶች ኪራይ ጨረታ ተጫራቾች በሙሉ
1. የመጨረሻው የጨረታ አሸናፊዎች ውጤት ይፋ የተደረገ ሲሆን አጠቃላይ ውጤቱም በሁሉም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና በዋናው መ/ቤት የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ የተለጠፈ በመሆኑ ከ12/07/2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት በጨረታ ሒደቱ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተጫራቾች በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የሪከርድና ማህደር አገልግሎት ቢሮ በአካል በመቅረብ ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
2. የጨረታ አሸናፊዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ12/07/2014 ዓ.ም ጀምሮ ከአስራ ሁለት ተካታታይ ቀናት በኋላ ባሉት አስር ተከታታይ ቀናቶች ቤቶቹ በሚገኙበት የቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ውል መዋዋል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
3. CPO መመለሻ ቀን በተመለከተ ውጤቱ ይፋ ከተደረገበት ከ12/07/2014 ዓ.ም ጀምሮ አስር ተከታታይ ቀናት በኋላ ቤቶቹን በተጫረታችሁባቸው የቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
.
የ 3ኛ ዙር የ157 የንግድ ቤቶች ኪራይ ጨረታ አጠቃላይ ውጤት ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው መተግበሪያ በመግባት የሁሉንም የንግድ ቤቶች ውጤት ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የመተግበሪያ ሊንክ – http://www.fhc.gov.et:7098/hubd
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
የተሟላ፣ትኩስ እና አስተማማኝ ኮንዶሚንየም እና ሪልስቴት ነክ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.condoaddis.com/ ፌስቡክ፡- https://wwww.facebook.com/condoadis ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/CondominiumforsaleinAddisAbaba1
ቴሌግራም፦ https://t.me/condoaddis በመወዳጀት ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!