በአዲስ አበባ ከ143 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ ነው

.
በአዲስ አበባ በ40/60 እና በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም በነባር ግንባታ 139 ሺህ 008 ቤቶች እንዲሁም በ2012 በጀት ዓመት የተጀመሩ 4 ሺህ 287 ቤቶች በአጠቃላይ 143 ሺህ 295 ቤቶች በግንባታ ላይ እንደሚገኙ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።
.
 የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊዎች እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ህዳር 7/2014 በተለያዩ የቤት ልማት አማራጮች በከተማ አስተዳደሩ እየተገነቡ የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን አፈጻጸም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
.
በአመራሮቹ ከተጎበኙት ሳይቶች መካከል ቦሌ አራብሳ፣ ቦሌ አያት፣ መገናኛ እንዲሁም በ2012 በጀት ዓመት የተጀመሩ አዳዲስ የ40/60 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተጠቃሽ ሲሆኑ፣ የፕሮጀክቶችን አፈጻጸም በተመለከተ በፕሮጀክቶቹ ሥራ አስኪያጆች ማብራሪያ ተሰጥቷል።
.
በከተማ አስተዳደሩ በግንባታ ላይ ከሚገኙት 143 ሺህ 295 ቤቶች መካከል 101 ሺህ 594 ቤቶች 20/80 እንዲሁም 41 ሺህ 261 ቤቶች በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም እየተገነቡ የሚገኙ መሆናቸውም ተገልጿል።
.
በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም 107 ሺህ 768 ቤቶችን እስከ የካቲት 30/2014  ግንባታቸውን ለማጠናቀቅ ዕቅድ የተያዘ ሲሆን አፈጻጸሙ 97 ነጥብ 86 በመቶ መድረሱ ተገልጿል።
.
በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ደግሞ እስከ የካቲት 30/2014 38 ሺህ 240 ቤቶችን የግንባታ ሥራቸውን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ሲሆን አሁናዊ አፈጻጸሙ 92 ነጥብ 24 በመቶ ላይ እንደደረሰ ተጠቁሟል።
.
የሲሚንቶ እጥረት፣ የሲሚንቶ ግብአት ዋጋ መጨመርና የፋብሪካዎች አቅርቦት በበቂ ሁኔታ አለመኖር፣ የመሰረተ ልማት ተቋማት ተቀናጅቶ አለመስራት፣ የሥራ ተቋራጮች የአቅም ክፍተት እና የወሰን ማስከበር ችግር እንዲሁም የፋይናንስ እጥረት መኖር ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዳይጠናቀቁ እንቅፍት እንደሆነባቸው ሥራ ተቋራጮች በጉብኝቱ ወቅት አንስተዋል።
.
በጉብኝቱ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ያስሚን ውሀብረቢ፤ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የቤት ልማት አማራጮች በርካታ ዝቅተኛ የማህበረሰብ ክፍሎችን የቤት ባለቤት ማድረግ መቻሉን ጠቁመው፣ በከተማ አስተዳደሩ በመገንባት ላይ የሚገኙ ቤቶች ላይ የሚታዩ ችግሮችን በጋራ ሆነን በመቅረፍ ቤቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለነዋሪዎች ለማስተላለፍ በትኩረት እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
.
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሊድ አብዱራህማን በበኩላቸው፣ የቤት ልማት ፕሮግራሙ የቤት ችግርን ከመቅረፍ ባለፈ የተለያዩ ድርብ ዓላማዎችን ይዞ የተቀረጸ መሆኑን አንስተው እየገነባን ያለነው ከተማን በመሆኑ ውጤታማ እንሆን ዘንድ ተቀናጅተን ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
.
በጉብኝቱም ሥራ ተቋራጮች፣ ከውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን፣ ከመንገዶች ባለስልጣን፣ ከመብራት ኃይል፣ ከባንክ እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች መሳተፋቸውን ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

addismaleda

https://bit.ly/3lg1G9r

የተሟላ፣ትኩስ እና አስተማማኝ ኮንዶሚንየም እና ሪልስቴት ነክ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.condoaddis.com/ ፌስቡክ፡- https://wwww.facebook.com/condoadis ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/CondominiumforsaleinAddisAbaba1
ቴሌግራም፦ https://t.me/condoaddis በመወዳጀት ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top