አስቸኳይ ለነባር የ20/80 እና የ40/60 የማህበር ቤት ፈላጊዎች

  አስቸኳይ ለነባር 20/80 እና 40/60 የማህበር ቤት ፈላጊዎች

በህብረት ስራ ማህበር ለመደራጀት የተመዘገቡ 20/80 እና 40/60 ቤት ፈላጊዎች ወደ ተግባር ለማስገባት ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡


የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፍላጎት ያላቸውን ነባር 20/80 እና 40/60 የማህበር ቤት ፈላጊዎችን በህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው እንዲሰሩ በኦንላይን ምዝገባ ማካሄዱ የሚታወቅ ነው፡፡


ቢሮውም ካሉት አማራጭ የቤት አቅርቦት ውስጥ አንዱ የሆነውን የማህበር ቤት ተግባራዊ ለማድረግ የዲዛይን ዝግጅት የመሬት ዝግጅት እና የአበዳሪ ባንኮችን የመለየት ቅድመ ሁኔታዎችን በማጠናቀቅ ማህበራቱ ተደራጅተው ወደ ተግባር የሚገቡበትን ሁኔታ ማመቻቸቱን አሳውቋል፡፡


የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮም በኦንላይን የተመዘገባችሁ 20/80 እና 40 /60 ቤት ፈላጊዎች አስፈላጊውን መረጃ እንድታሟሉ ሲል ጠይቋል፡፡


በመሆኑም ከዚህ በፊት በኦንላይን የተመዘገባችሁ የማህበር ቤቱ ፈላጊዎች ሁሉበአዲስ አበባ ከተማ በራሳችሁም ሆነ በትዳር አጋራችሁ ስም ቤት ወይም ቤት መስሪያ ቦታ የሌላችሁ ወይም ኖሯችሁ 1997 . ወዲህ በስጦታ ወይም በሽያጭ ያላስተላለፋችሁ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃየሚገልፅ ቅፅ ከምትኖሩበት ወረዳ ቤቶች አስተዳደር /ቤት በመውሰድ ከየካቲት 16 እስከ መጋቢት 16 / 2014 . ድረስ በኦንላይን የተደረገውን ምዝገባ በአካል እንድታረጋግጡ ብሏል፡፡


ቢሮው ሁሉም ተመዝጋቢ ከላይ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማስረጃውን ማቅረብ እንደሚጠበቅበትና ጊዜውን አሳልፈው ለሚመጡ ኃላፊነት እንደማይወስድ አሳስቧል።
 

የተሟላ፣ትኩስ እና አስተማማኝ ኮንዶሚንየም እና ሪልስቴት ነክ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.condoaddis.com/ ፌስቡክ፡- https://wwww.facebook.com/condoadis ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/CondominiumforsaleinAddisAbaba1
ቴሌግራም፦ https://t.me/condoaddis በመወዳጀት ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top