Condoaddis

የመሬት ነክ አገልግሎት እግድ ተነሳ news


በአዲስ አበባ ከተማ ተወስኖ የነበረው የመሬት ነክ አገልግሎት እግድ ተነሳ

  
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እንደዘገበው በመዲናዋ አስተዳደር በጊዜያዊነት ታግዶ የነበረው የመሬት ነክ አገልግሎት እግድ መነሳቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ ብሏል::
 
ጊዜያዊ እግዱ የተነሳ በመሆኑ አገልግሎቱን ከጥር 13 / 2014 ጀምሮ በየክፍለ ከተማው መስተናገድ እንደተጀመረ ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ከነሐሴ 7 ቀን 2013 ጀምሮ በጊዜያዊነት ታግደው የነበሩና እግዱ ከተነሳላቸው አገልግሎቶች መካከል ÷ ህጋዊ ሰነድ ላላቸው ይዞታዎች ብቻ ዋስትና እዳ መመዝገብ፣ የፍርድ ቤት እና የባንክ እግድ የመመዝገብና የመሰረዝ አገልግሎት (የእዳና እገዳ የማጣራት አገልግሎት)፣ የስመ ንብረት ዝውውር ስራ(በባንክ ሐራጅ የተሸጠ፣ በፍ/ቤት አፈፃፀም የተሸጠ፣ የኮንዶሚኒየም ቤት የስም ዝውውር አገልግሎት፥ እንዲሁም በውርስ የተላለፈ ንብረት እና በሪል እስቴትስ አልሚ የተፈፀመ የቤት ሽያጭ ይጠቀሳሉ፡፡
 
በተጨማሪም ለነባር ይዞታዎች የቦታ ኪራይና የቤት ግብር ተመን፣ የንብረት ግመታ፣ በይዞታ ይገባኛል ክርክር ፣ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማስረጃ መስጠት፣ የወሰን ይመላከትልኝ /የወሰን ችካል/፣ በከተማ አስተዳደር የሚታወቅ እና ቅድሚያ የሚሰጥ የልማት ተነሺ አገልግሎት (ካሣ ክፍያ፣ ምትክ ቤት እና ምትክ ቦታ አሰጣጥ አገልግሎቶች) ጊዜያዊ እግድ ከተነሳላቸው አገልግሎቶችም እግዱ የተነሳላቸው አገልግሎቶች ናቸው፡፡
 
እንዲሁም የቦታ ዝግጅት፣ የወሰን ማስከበር ተግባራት፣ በሊዝ በተላለፈ ቦታ ላይ የግንባታ ክትትል፣ የለማ መሬት በምደባ ወይም በጨረታ ማስተላለፍ፣ አዲስ ካርታ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች (የምትክ ኮንዶሚኒየም ቤት ለተወሰነላቸው፣ ለአመራር የሚሰጡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች እና የሪል እስቴትስ ተጠቃሚዎች /ቤት ገዥዎች የተናጠል ካርታ/መሆናቸውን አገልግሎቶች ጊዜያዊ እግዱ ተነስቶላቸዋል፡፡
 
 የተሟላ፣ትኩስ እና  አስተማማኝ ኮንዶሚንየም እና ሪልስቴት ነክ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.condoaddis.com/
ፌስቡክ፡- https://wwww.facebook.com/condoaddis
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/CondominiumforsaleinAddisAbaba1
ቴሌግራም፦ https://t.me/condoaddis
በመወዳጀት
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

የተሟላ፣ትኩስ እና አስተማማኝ ኮንዶሚንየም እና ሪልስቴት ነክ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.condoaddis.com/ ፌስቡክ፡- https://wwww.facebook.com/condoadis ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/CondominiumforsaleinAddisAbaba1
ቴሌግራም፦ https://t.me/condoaddis በመወዳጀት ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Please follow and like us:
Exit mobile version