የኮንዶሚኒየም የንግድ ቤቶች ጨረታ ማስታወቂያBy Condoaddis / July 26, 2022 የኮንዶሚኒየም የንግድ ቤቶች ጨረታ ማስታወቂያየአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በከተማ አስተዳደሩ በ20/80 ፕሮግራም በቦሌ ቡልቡላ በለሚ ኩራ፣ በአራዳ፣ በአቃቂ ቃሊቲ እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ያስገነባቸውን 2,667 ኮንዶሚኒየም የንግድ ቤቶች በጨረታ አወዳድሮ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ኮርፖሬሽኑ ለሽያጭ ያቀረባቸውን የንግድ ቤቶች በጨረታ ተወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት የጨረታ ሰነዱን ከሃምሌ 11 እስከ ነሃሴ 04/2014 ዓ.ም ድረስ ባሉት 21 (ሃያ አንድ) የስራ ቀናት፣ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡10 እስከ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡30 እስከ 6፡00 ድረስ የማይመለስ 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ) ብር በመክፈል ሰነዱን ከሚከተሉት አድራሻዎች መግዛት ይችላል። የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግ/ማ ጋር በገባው ውልየጨረታ ሰነድ መሸጫ ሥፍራዎች መሰረት የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው በ9 (ዘጠኝ) የተለያዩ የኮሜርሻል ኖሚኒስ ቅርንጫፎች ሲሆን አድራሻቸው እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡፡✓ የጨረታ ማጠናቀቂያ ቀን፦ ነሃሴ 04/2014 ዓ.ም እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡የጨረታ መክፈቻ ቀን፡- ከነሃሴ 05/2014 ዓ.ም እስከ ነሃሴ 17/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው ፕሮግራም መሰረት ይሆናል፡፡✓ ማሳሰቢያ፡- ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶቸ ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንስልክ ቁጥር0111-55-98-610111-57-79-830114-42-57-830114-66-36-36ፒያሳ አራዳ ህንፃ 1ኛፎቅሳሪስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንጻ (ሪየስ ኢንጂነሪንግ ፊት ለፊት) ወይም ቀይ መስቀል መድኃኒት ቤት ጎንልደታ ማርያም ቤ/ክ ከፍ ብሎ ዛግዌ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊት ለፊትላምበረት ሾላ ወተት ፋብሪካ ፊት ለፊት የሚገኝ0116-68-31-02011384-20-00የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ የሚገኝበት ህንፃደንበል ሲቲ ሴንተር ጀርባበአማራጭነት በቴሌግራም ቻናላችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።👇👇👇👇👇t.me/condoaddisእንዲሁም፦Facebook.com/condoadis Please follow and like us:
i need 14th round condomimu shop result
thanks
we will send you after you pay birr 500