Condoaddis

ለ14ኛ ዙር 20/80 እና 3ኛ ዙር 40/60 ዕድለኞች

6ሺህ 938 እድለኞች እስካሁን ቀርበው ውል አልተዋዋሉም ተባለ

የአዲስ አ/አ ቤቶች ኮርፓሬሽን በ20/80 ለ14ኛ ዙር ፣ በ40/60 ለ3ኛ ዙር የጋራ መኖሪያቤት አጣ ወጥቶላቸው ውል እንዲዋዋሉ ከጥር 1/2015 ዓ.ም. ጀምሮ ቦሌ ክ/ከተማ ውስጥ በሚገኘው የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ በመምጣት ቅፅ 09 ወደ መኖሪያ ቀበሌዎች ወስደው አስሞልተው ለማምጣት ቀርበው የወሰዱ 25,703 ሲሆኑ የቀበሌውን ቅፅ 9 አስሞልተው በመመለስ ቅፅ 03 ወደ ባንክ ቀርበው መውሰድ የሚገባቸው ሰዎች ብዛት 25,353 ሰዎች ናቸው።

ይሁን እንጂ ቅፅ 03 ትን እስካሁን የወሰዱት 22,235 ናቸው ይህም በመቶኛ ሲሰላ 87.71% ነው ።

ከእነዚህ መካከል የባንኩን ሂደት ጨርሰው ወደ አንድ ማእከል ተመልሰው እስከ መጋቢት 25/2015 ዓ,ም. ድረስ ውል የተዋዋሉ በ20/80 እድለኞች ቁጥር 16,617 ሰዎች ፣ በ40/60 እድለኞች 2,218 ሰዎች ሲሆኑ በአጠቃላይ በሁለቱም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮግራም አስካሁን ውል የፈፀሙት 18,835 ሰዎች ብቻ ናቸው ። ይህም ማለት መዋዋል ካለባቸው 25,773 ሰዎች መካከል 6,938 ሰዎች እስካሁን ቀርበው ውል አልተዋዋሉም ማለት ነው ። የባንኩን ቅፅ 03 ወስደው እስካሁን ውል ያልተዋዋሉ ደግሞ 3,400 ሰዎች ናቸው ።

ከጥር 1/2015 እስከ መጋቢት 25/2015 ዓም ድረስ አስፈላጊውን ፕሮሰስ ጨርሰው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲሰራላቸው የተላኩ በ20/80 እድለኞች ብዛት 15,836 ሰዎች በ40/60 እድለኞች ብዛት 1,235 ሰዎች በአጠቃላይ ለካርታ የተላኩ 17,071 ሰዎች ብቻ መሆናቸውን የኮርፓሬሽኑ የቤት ማስተላለፍ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ካሳሁን ዘውዴ አስታውቀዋል። በዚህ መሰረት ወደ ካርታ ስራ ያልተላኩ 8,702 ፋይሎች ይቀራሉ ማለት ነው ።

እንደ ዳሬክተሩ ገለፃ በሁለቱም የቤት ልማት ፕሮግራሞች ከ25,773 ሰዎች ውላቸውን ተዋውለው ካርታቸውን ሊወስዱ እንደሚገባ ጠቁመው ካለው ቁጥር አንፃር ሲታይ በተለያዩ ምክንያቶች ቀርበው ያልተዋዋሉ እንዳሉ ጠቁመዋል ።

እንደሚታወቀው የውል መዋዋያ ጊዜው ላለፉት 3 ወራት ማለትም ከጥር 1/2015 ጀምሮ እስከ መጋቢት 26/2015 ድረስ ብቻ እንደሆነ የገለፁት ዳይሬክተሩ በተቀመጠው መርሀግብር መሰረት የውል ጊዜው መጋቢት 26/2015 ያበቃል ። አምስት ቀን (5) የመክፈያ ጊዜ ብቻነው ከዚህ በኃላ የሚቀረው ስለሆነም ወደ 6938 ሰው ገና ያልተዋዋሉ አሉ በዚህ መካከል በፕሮሰስ ላይ ያሉትን ጨምሮ ገና በርካታ ሰዎች በሂደት ላይ ያሉ መሆናቸውን ኮርፓሬሽኑ ስለተረዳ የውል ማዋዋሉ ሂደት ለአንድ ወር እንዲራዘም መጠየቃቸውን ገልፀዋል ።

የቤት እድለኞች መገንዘብ ያለባቸው አሁን በጠየቁት የውል መዋዋያ ይራዘምልን ጥያቄ መሰረት አንድ ወሩ ከተፈቀደ በተሰጣቸው እድል ቀርበው መዋዋል ካልቻሉ በመመሪያው መሰረት ቤቱን እንዳልፈለጉት ተቆጥሮ ለመንግስት ተመላሽ ስለሚሆን ባለ እድለኞች አሁንም ወደ አንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ በመምጣት እንዲዋዋሉ ጥሪ አቅርበዋል ።

__________
በገጻችን የምናቀርባቸውን መረጃዎች በአማራጭነት በፌስቡክ ቻናላችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
👇👇👇👇👇
F.me/condoadis
እንዲሁም፦
T.me/condoadis

 

Please follow and like us:
Exit mobile version