2ኛ ዙር የመሬት ጨረታ አሸናፊዎች ይፋ ሆኑ

2ኛ ዙር የመሬት ጨረታ ውጤት

  •  በአንድ ካሬ ሜትር አሸናፊ የሆነው ከፍተኛ ዋጋ 470 ሺህ ብር ሲሆን ዝቅተኛ 20 ሺህ 100 ብር ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የ2ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ታትሞ ተሰራጭቷል።

በጨረታው ዝቅተኛ ዋጋ የተመዘገበው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ሲሆን ይህም በካሬ ሜትር 20 ሺህ 100 ብር ነው።

ከፍተኛው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በካሬ ሜትር 470 ሺህ ብር እንደሆነ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በካሬ ሜትር 470 ሺህ ብር ያቀረበው ” ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ት/ቤት ” መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአሸናፊዎች ዝርዝር ላይ ተመልክቷል።

በአጠቃላይ 4 ሺህ 201 ተጫራቾች የጨረታ ሰንድ በኦንላን መግዛታቸው ተነግሯል። ከነዚህ ውስጥ 2 ሺ 972 ሰነዶች ተሟልተው ተመላሽ እንደተደረጉ ተገልጿል።

1ኛ የወጡ አሸናፊ ተጫራቾች በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ኤም.ኤ ህንጻ  ላይ የአዲስ አበባ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ የሊዝ ውል እንዲፈጽሙ ጥሪ ቀርቧል።

1ኛ የወጡ ተጫራቾች ውል የማይፈጽሙ ከሆነ ዕድሉ 2ኛ ለወጡት ተጫራቾች ተላልፎ ይሰጣል።

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top