ስለ 1997 እና 2005 ኮንዶሚንየም ተመዝጋቢዎች መረጃ

🔈#የነዋሪዎችድምጽ

” ተስፋ ቆርጠናል ” – ቆጣቢዎች

በአዲስ አበባ የነዋሪውን የቤት ችግር ለመፍታት በሚል መንግስት የጋራ መኖሪያ ቤት ወይም የኮንዶሚንየም ቤት ምዝገባን በ1997 እና 2005 ያደረገ ሲሆን እጣው የዘገየባቸው ነዋሪዎች ” ተስፋ ቆርጠናል ” ሲሉ ገለጹ።

ነዋሪዎቹ ቃላቸውን የሰጡት #ለአሃዱ ነው።

ከተመዘገቡ 19 እና 11 ዓመታት እንዳለፋቸው የተናገሩት ተመዝጋቢዎች ” ከወደ መንግስትም ምንም አይነት መረጃ እየወጣ አለመሆኑ ጥያቄ ፈጥሮብናል ” ብለዋል።

” የሚመለከተው አካል በአፋጣኝ ምላሽ ይስጠን ” የሚሉት ተመዝጋቢዎቹ ” በመንግስት በኩል ቅድሚያ እየተሰጣቸው ያሉ ነገሮች ተመዝጋቢዎቹ ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ከግንዛቤ ያስገባ አይደለም ” ሲሉ ተናግረዋን።

ለአብነትም ከወራት በፊት የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን 3 ሺህ የሚሆኑ ቤቶችን በመግንባት ለሽያጭ ማቅረቡን በማስታወስ ” ለምን እንዲህ ይደረጋል ? የሚል ጥያቄ ብናቀርብም ሰሚ አልነበረም ” ብለዋል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ምን አለ ?

ኮርፖሬሽኑ ” አትቆጥቡ ያለ አካል የለም ከመንግስት በሚቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ግንባታዎች እየተካሄዱ ነው ” ብሏል።

 

” ተመዝጋቢዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ ” ሲልም ጠይቋል።

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top