የቤት ግብር ማሻሻያ ተግባራዊ እንዲደረግ ስለማሣወቅ

የቤት ግብር ማሻሻያ ተግባራዊ እንዲደረግ ስለማሣወቅ

የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ በቁጥር ፋ/ቢ/2/64/2249 በተን 3/3/2015 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ በከተማችን እያደገ የመጣውን የአገልግሎት ፍላጐት እና የመሠረተ ልማት አቅርቦት ችግሮችን ከመፍታት አንፃር ገቢን አሟጦ መሰብሰብ ማስፈለጉን ገልጾ የቦታ ኪራይና የቤት ግብር ግመታ ወቅታዊ ባለመደረጉ ከዚህ ዘርፍ የሚሰበሰበው ገቢ እጅግ አነስተኛ መሆኑና ችግሩን ለመፍታት ከባለድርሻ ተቋማት የተውጣጣ የንብረት ግብር ማስተግበሪያ ጊዜያዊ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በማቋቋም ወደ ሥራ መገባቱን አሣውቆናል፡፡

በመሆኑም ጊዜያዊ ፕ/ጽ/ቤቱ አሁን ያለውን ዓመታዊ የቤት ግብር ግምት ለማሻሻል የዳሰሣ ጥናት በማቅረብና በተገኘው የጥናቱ ውጤቶች ላይም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አቅጣጫ የተሰጠበት በመሆኑ የገቢዎች ቢሮ የመሬት ተቋማት በሚልኩት የግብር ግምት መሠረት የቤት ግብሩ እንዲሰበስብ የተወሰነ በመሆኑ፣ በአድራሻ የተገለፀላችሁ ዘርፍና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወደ ተግባር እንድትገቡ የጥናት ውጤት ውሣኔውን እና አባሪ ደብዳቤውን 6 ገጽ ከዚህ ደብዳቤ ጋር በማያያዝ የላከን መሆኑን እገልፃለሁ፡፡

ከሰላምታ ጋር

 

ተያያዥ ሠነዱን ይመልከቱ

👇👇👇

የቤት ግብር ማሻሻያ (1)(1)

 

 

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top