Site icon Condoaddis

ለጋራ ህንፃ መ/ቤት/ህ/ሥራ/ማህበር በፍቃደኝነት ለተደራጅታችሁ ጥሪ ቀረበ

ለጋራ ህንፃ መ/ቤት/ህ/ሥራ/ማህበር በፍቃደኝነት ለተደራጅታችሁ ጥሪ ቀረበ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቤቶች ልማትና አስተደዳር ቢሮ የ2005 ዓ.ም በ20/80 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝግባችሁ አሁን መንግስት ባመቻቸው የጋራ ህንፃ መ/ቤት/ህ/ሥራ/ማህበር በፍቃደኝነት ተደራጅታችሁ ቤት ለመገንባት የተመዝግባችሁና አሰፈላጊውን መረጃ አሟልታችሁ ስም ዝርዝራችሁ በግሩፕ ተደልድሎ ለህብረት ሥራ ማህበራት ኤጀንሲ የተላከ መሆኑ ይታወቃል።

ይሁንና ከየግሩፕ አስተባበሪዎች አድራሻቸውን ማግኘት ያልቻልን ተመዝጋቢዎች በሙሉ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ማስታወቂያዎች በአካል ቀርባችሁ መረጃ እንድትሰጡ ብትጠየቁ እና ቀርበው ሪፖርት እንድታደርጉ ብትባሉ ሪፖርት ያላደረጋችሁ አባላትን እና በተለያየ መልኩ ቅድመ ክፍያውን መክፈል አንችልም ያላችሁ የመተካካት ስራ በቢሮው በኩል እንዲሰራ በሚል ውሣኔ መሰረት ተቋሙ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል:-

1. B+G+9 የህንፃ ከፍታ ላይ 42 የነበረው የቡድን ድልድል ቡድን 1፣2እና 3 የታጠፈ መሆኑንና በነዚህ ቡድን የነበራችሁ ተመዝጋቢዎች ድልድሉን በማየት ወደ ተመደባችሁበት ቡድን አስተባባሪዎች ሪፖርት እንድታደርጉ፤

2. የ2B+G+13 የነበረው 15 ቡድን ባላችሁበት ሲሆን ተጠባባቂዎችን ሙሉ ለሙሉ በክፍት ቦታዎች ላይ በመደልደል የተሟላ መሆኑን፤

3. ተጠባባቂ የነበራችሁ ተመዝጋቢዎች 2B+G+13 ላይ ሙሉ ለሙሉ የተመደባችሁ በመሆኑ ስም ዝርዝርራችሁን በማየት ለቡድን አስተባባሪዎች ሪፖርት እንድታደርጉ በB+G+9 በተጠባባቂነት የነበራችሁ ዝርዝራችሁን በቅደም ተከተላችሁ መሠረት ፖስት የምናደረግ በመሆኑ ያልተመደባችሁ በትዕግስት በተጠባባቂነት እንድትቆዩ እናስታውቃለን፤

በመጨረሻም ከቢሮው እና ከህብረት ሥራ ማህበራት ኤጀንሲ ውጪ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎችን መከተል እንደሌለባችሁ እና ቢሮው በህጋዊ መንገድ ኃላፊነት ወስዶ ከሚለቃቸው መረጃዎች ውጪ በተዛባ መረጃ እንዳትሳሳቱ እናሳስባለን ፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

ሙሉ ስማችሁን ከታች ባለው ሊንክ መመልከት ትችላላችሁ
👇👇

Group B+G+9(1)

Group 2B+G+13

Please follow and like us:
Exit mobile version