የጋራ መኖሪያ ቤት ደርሷቸው እስካሁን ወደ ቤታችው ያልገቡ ነዋሪዎች ማሳሰቢያ ተሰጠ

የጋራ መኖሪያ ቤት ደርሷቸው እስካሁን ወደ ቤታችው ያልገቡ ነዋሪዎች እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ድረስ መግባት እንዳለባቸው ቢሮው እና ኮርፖሬሽኑ አሳሰቡ

የጋራ መኖሪያ ቤት ደርሷቸው እስካሁን ወደ ቤታችው ያልገቡ ነዋሪዎች እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ድረስ ወደ ቤታቸው መግባት እንዳለባቸው ያሳሰቡት በቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው እንዳሉት ከፍሳሽ ፣ ከመንገድ፣ ከውሃና ከኤሌትሪክ እንዲሁም ከሳይት ወርክ አንፃር የተመረጡ ስራዎች ፣ ከሊፍት ገጠማና የውሃ ፓንፕና የሮቶ ተከላ ስራዎችን እየተፈተሸ የተጓደሉትን ለማስተካከል ቢሮው እና ኮርፖሬሽኑ ሌት ተቀን እየሰሩ ሲሆን ነዋሪዎችንም የአስተዳደሩ ፍላጎትን በመረዳት በራሳቸው አቅም መሰራት የሚችሉትን ስራዎች ወደየ ሳይቶቹ በመሔድ የማስተካከል ስራዎች መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል ፡፡

ነዋሪው ወደ የመኖሪያ ሳይቱ በጊዜ ባለመግባቱ ምክንያት እየደረሰ ያለውን ችግር በውል በመረዳት እያጋጠሙ ላሉ ችግሮችን ለመፍታት የመፍትሄ አካል በመሆንና መኖሪያ መንደራችውን በማልማት ለኑሮ ምቹና ጽዱ በማድረግ በከተማ ገፅታ ግንባታ ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ አሳስበዋል ።

ቀበሌ ቤቶችን ጨምሮ ሌሎችንም የመንግስት ቤቶችን ይዘው የተቀመጡ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕድለኞች ቤቶቹን ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ማስተላለፍ እንዲቻል ከሰኔ ሰላሳ አስቀድመው መልቀቅ እንደሚጠበቅባቸው ያመላከቱት ዋና ዳይሬክቴሩ ዕድለኞቹ የአካባቢ ጽዳትና ውበት ስራን ጨምሮ የጸጥታ ስራዎችን በአካባቢው ከሚገኙ የጸጥታ ተቋማት ጋር መከወን እንዲቻል አስቀድመው መግባት ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል ።

በቀጣይም ከተማ አስተዳደሩ በቅሩቡ ይፋ የተደረገውን የ70/30 የጋራ መኖሪያ ቤት አማራጭን ጨምሮ በከተማዋ የቤት ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም ይሰራልም ብለዋል።

__________
በገጻችን የምናቀርባቸውን መረጃዎች በአማራጭነት በቴሌግራም ቻናላችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
👇👇👇👇👇
t.me/condoaddis
እንዲሁም፦
Fb.me/condoadis

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top