Condoaddis

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያን ባለስልጣን ሃና ተኸልኩን ዋና ዳይሬክተር አድርጎ ሾመ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያን ባለስልጣን ሃና ተኸልኩን ዋና ዳይሬክተር አድርጎ ሲሾም በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ብሩክ ታዬን (ዶ/ር) ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርጎ ተቀብሏል

ላለፉት ሁለት ዓመታት የካፒታል ገበያ ባለስልጣንን ከማቋቋም ጀምሮ በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ በነበሩት ብሩክ ታዬ ( ዶ/ር)  ምትክ በህግ እና በኢኮኖሚያዊ ወንጀሎች ላይ ሰፊ ልምድ ያላቸውን ሃና ተኸልኩን አዲሱ ዳይሬክተር አድርጎ መቀበሉን አስታዉቋል ።

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የመጀመሪያ እና የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ብሩክ ታዬ ( ዶ/ር) በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዉ መሾማቸው ተሰምቷል።

ብሩክ ታዬ የኢትዮጵያ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ 27 የሚደርሱ የመንግስት ኩባንያዎችን የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግን ላለፉት ሁለት ዓመታት በስራ አስፈፃሚነት በመሩት አብዱረህማን ኢድ ጣሂር ምትክ መሾማቸው ለማወቅ ተችሏል ።

Please follow and like us:
Exit mobile version