የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮ ለመከፈት የሚፈልጉ የሥራ ፈቃድ መስጠት መጀመሩን አስታዉቋል!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮ ለመከፈት የሚፈልጉ የሥራ ፈቃድ መስጠት መጀመሩን አስታዉቋል

በገበያ ላይ ተመሥርተው የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ መሸጥና መግዛት የሚፈልጉ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች እንዲቋቋሙ በተፈቀደው መሠረት ብሔራዊ ባንክ ይህኑ ፍቃድ መስጠት ጀምሬያለሁ ብሏል።

የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች መቋቋም የውጭ ምንዛሪ ገበያን መሠረት ለማስፋትና ለማጠናከር እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ ለመሸጥም ሆነ ለመግዛት የሚሹ ደንበኞችን ፍላጎት ለማሳካት እንደሚረዳ ይታመናል ብሏል ባንኩ ባወጣዉ መግለጫ ።

የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች እንዲከፈቱ የሥራ ፈቃድ መስጠት መጀመሩን የገለፀው ባንኩ ይህ እርምጃ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ለመክፈትና ዘርፉን በቀጣይ ዓመታት ተወዳዳሪ ለማድረግ የተጀመርነው አዲስ ምዕራፍ መሆኑ ገልጿል።

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top