የአፍሪካ ልማት ባንክ ለዓለም አቀፍ ንግድ ልውውጥ ዋስትና የሚውል 40 ሚሊዮን ዶላር ለዳሸን ባንክ አፅድቋል።

#Afdp #DashenBank
የአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን ዳይሬክተሮች ቦርድ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ የመጀመሪያ የሆነውን ለዓለም አቀፍ ንግድ ልውውጥ ዋስትና የሚውል 40 ሚሊዮን ዶላር ለዳሸን ባንክ አፅድቋል።

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ባንካችን የአፍሪካ ልማት ባንክ ያስቀምጣቸውን ጥብቅ ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላቱ ይህ 40 ሚሊዮን ዶላር የንግድ ፋይናንስ ልውውጥ ዋስትና ማዕቀፍ በመፈቀዱ በጣም ደስተኞች ነን። ይህም ባንካችን በክፍለ አህጉሩና ከዚያም ባለፈ የንግድ አገልግሎታችንን ለማሳደግ በጣም  አስፈላጊ ድጋፍ ነው ብለዋል።

ይህን  ድጋፍ ለማግኘት ያሟላቸው ቅድመ ሁኔታዎች እና በሂደቱ የተገኙ የልምድ ልውውጦች ዳሸን ባንክ ከአፍሪካ ተመራጭ እና ቀዳሚ ባንኮች ተርታ ለመሰለፍ ያለውን ራዕይ ዕውን ለማድረግ እንደ ግብአት እንደሚጠቅም አመልክተዋል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ቢሮ ዳይሬክተር ጀነራል ኔና ኑዋቡፎ በበኩላቸው የአፍሪካን ንግድ መደገፍ ባንካችን ተቀዳሚ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው። ይህም የአህጉሩን የኢኮኖሚ ዕድገት ለመጨመርና ድንበር ዘለል ንግድ ለማሳደግ ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል።

ባንኩ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ያገኘው ይህ የድጋፍ ማዕቀፍ ባንኩ በዓለም አቀፍ ንግድ ልውውጥ ያለውን ተቀባይነት እና ተመራጭነት ይበልጥ እንደሚያሳድገው ተመልክቷል።

የፋይናንስ አቅርቦቱ ዳሸን ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ተቋማት እንዲሁም ሌሎች አገር በቀል ድርጅቶች ምርት ለመላክና ለማስመጣት የሚፈልጉትን አቅርቦትና ዋስትና እንዲያገኙ ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።

የገንዘብ አቅርቦቱ ለኢትዮጵያ በጣም አስፈላጊ የሆኑ እንደ ማዳበሪያ፣መድሃኒት፣የሶላር ሃይል ማመንጫ፣የግብርና ማሽነሪዎችና ሌሎች ምርቶችን ለማስገባት ያግዛል።

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top