በብሔራዊ ባንክ ተመን የአንድ ግራም ወርቅ ዋጋ ስንት ደረሰ?


ብሄራዊ ባንክ እለታዊ የወርቅ መግዣ ዋጋ ይፋ በማድረግ ላይ ይገኛልብሔራዊ ባንክ ወርቅ የሚገዛው በዓለም አቀፍ እለታዊ ዋጋ መሆኑን አስታውቋል

ብሔራዊ ባንክ ከምንዛሬ ስርአት ለውጥ በኋላ ወርቅ የሚገዛው በአለምአቀፍ እለታዊ ዋጋ መሆኑን መግለጹን ተከትሎ እለታዊ የወርቅ መግዣ ዋጋ በድረ ገጹ ይፋ እያደረገ ይገኛል።

በእየለቱ በምን ያህል የውጭ ምንዛሬ ወርቅ እንደሚገዛ በጽረ-ገጹ ይፋ እንደሚያደርግ የገለጸው ባንኩ፣የዛሬ የወርቅ መግዣ ዋጋን ይፋ አድርጓል።

ብሔራዊ ባንክ 1 ግራም ወርቅ በስንት ብር እየገዛ ነው?
በዚህም መሰረት ባለ 24 ካራት 1 ግራም ወርቅ 79.2074 የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባክ የምንዛሬ ዋጋ 8 ሺህ 834.4113 ብር እየገዛ መሆኑን አስታውቋል።

ባለ 23 ካራት 1 ግራም ወርቅ 75.9071የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባክ የምንዛሬ ዋጋ 8 ሺህ 466.3108 ብር እየገዛ መሆኑን የባንኩ መረጃ ያመለክታል።

ባለ 22 ካራት 1 ግራም ወርቅ 72.6068 የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባክ የምንዛሬ ዋጋ 1 ሺህ 098.2104 ብር እየገዛ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።

ባለ 21 ካራት 1 ግራም ወርቅ 69.3065 የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባክ የምንዛሬ ዋጋ 7 ሺህ 730.1099 ብር እየገዛ ይገኛል።

ባለ 20 ካራት 1 ግራም ወርቅ 66.0062 የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባንክ የምንዛሬ ዋጋ 7 ሺህ 362.0094 ብር እየገዛ መሆኑን ነው ባኩ በድረ ገጹ ያወጣው መረጃ ያሚያመለክተው።

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top