አሊባባ

♦አሊባባ
እ.ኤ.አ በ1999 በጃክ ማ የተመሰረተው አሊባባ ኩባንያ፡ የኢ-ኮሜርስ፣ የክፍያ ስርዓት፣ የገበያ መረጃና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ያካተተ ሁለገብ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው።

አሊባባ በቻይና ውስጥ የኢ-ኮሜርስ ለውጥ ያመጣ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃም ቢሆን በተለይም አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (SME’s) ወደ ገበያ እንዲደርሱ እና ስራቸውን እንዲያስፋፉ ረድቷል። ከዚህ በተጨማሪም የአሊባባ ሎጂስቲክስ በዓለም ደረጃ የሎጂስቲክስ ኢንዱስትሪውን እንደቀየረ ይታመናል።

በአሊባባ የቴክኖሎጂ ካምፓኒ ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከል የሚከተሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ :-

🥢 Alibaba.com – A B2B platform connecting global buyers and suppliers.

🥢 Taobao – A C2C platform similar to eBay, popular for a wide range of products.

🥢 Tmall – A B2C platform featuring branded products and stores.

🥢 Alipay – A mobile and online payment platform.

🥢 Alibaba Cloud – A cloud computing service provider.

አሊባባ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በርካታ የኤክስፖርት እድሎችን የሚፈጥር ሲሆን በተለይ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (SME’s) ምርታቸውን ወደ ገቢያ የሚያደርሱበትን መንገድ በማቅለል፣ የገበያ ተደራሽነታቸው በመጨመር፣ የምርትና አቅርቦት ሰንሰለት በማሳለጥ ረገድ መልካም የገበያ ሁኔታን እንደሚፈጥር ይታመናል።

በአንፃሩ በኢ-ኮሜርስ ፡ በክፍያ ስርዓት፣ በገበያ መረጃ አቅርቦት ፡ በሎጂስቲክስና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰሩ ፕላትፎርሞች (ድርጅቶች) በከባዱ እንደሚፈተኑም እሙን ነው፡፡

Alibaba ~ Open Sesame !

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top