ማስታወቂያ የጋራ መኖሪያ እና ንግድ ቤት ጨረታ 2ኛ አሸናፊዎች በሙሉ

ማስታወቂያ

የጋራ መኖሪያ እና ንግድ ቤት ጨረታ 2ኛ አሸናፊዎች በሙሉ

 

በአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የተገነቡ የመኖሪያና ንግድ ቤቶችን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በጋራ በመሆን ጨረታ በማውጣት እና ሂደቱን በማጠናቀቅ 1ኛ አሸናፊዎችን ሲያዋዋል የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

 

ይሁን እና በጨረታ ሰነዱ መመሪያ ክፍል ሁለት ተራ ቁጥር 28 እንደተገለፀው አንደኛ የወጣው አሸናፊ በተሰጠው ውል ጊዜ ተገኝቶ ካልተዋዋለ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ተወርሶ ሁለተኛ የወጣው ተጫራቾች አንደኛ አሸናፊ በሰጠው የካሬ ዋጋ ሊዋዋል እንደሚችል በመመሪያው ተገልጿል።

 

በዚህም መሰረት 2ኛ አሸናፊዎች ከነገ ማለትም ከነሀሴ 21/12/16 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት  አስፈላጊውን መረጃ በማሟላት ውል መዋዋል የምትችሉ መሆኑ እናሳውቃለን፡፡

 

በመሆኑም ባንቢስ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ግራውንድ ወለል ላይ የውል አገልግሎት መስጫ ማዕከል ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ  ስራዎች ቢሮ

Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top