Condoaddis

ስታንዳርድ ባንክ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ ሊጠይቅ ነዉ

ስታንዳርድ ባንክ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ ሊጠይቅ ነዉ

በደቡብ አፍሪካ መቀመጫዉን ያደረገው ስታንዳርድ ባንክ በአፍሪካ ትልቁን ያልተነካ ገበያ እየፈለገ በሚገኝበት በዚህ ጊዜ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት የባንክ ፍቃድ እንደሚጠይቅ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከሁለት ሳምንት በኃላ የኢንቨስትመንት የባንክ ፍቃድ ማመልከቻዎችን እንደሚቀበል ከቀናት በፊት መግለፁ አይዘነጋም ።

ለዉጪ ፋይናንስ ተቋማት በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ባንኮች ሆነው እንዲመዘገቡ የቀረበውን ጥሪ ተቀብሎ ፍቃደኝነቱን በማሳየት “ስታንደርድ ባንክ” ከቀዳሚዎቹ ተርታ መሰለፍ ችሏል።

በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ ለማግኘት ዝቅተኛው የተከፈለ ካፒታል ለዉጪ ባንኮች 100 ሚሊዮን ብር እና ከባንክ ላልሆኑ የፋይናንስ ተቋማት 25 ሚሊዮን ብር እንዲኖራቸው ይጠበቃል ።

ማንበብ ይቀጥሉ 👇👇👇
Condoaddis.com/category/etstocks

capital

Please follow and like us:
Exit mobile version