የ20/80 እና 40/60 ባለዕድለኞች ውል እንዲፈፅሙ ጥሪ ቀረበ።

የ20/80 እና 40/60 ባለዕድለኞች ውል እንዲፈፅሙ ጥሪ ቀረበ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የ14ኛ ዙር 20/80 እና 3ኛ ዙር 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤት እድለኞች ማሟላት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ከጥር 1ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ባሉት 60 የሥራ ቀናት ውስጥ ባለእድለኛው ወይም ወኪሉ ቀርበው ውል መዋዋል እንደሚጠበቅባቸው አሳስቧል።

ከተማ አስተዳደሩ በ14 ኛ ዙር የ2080 የቤት ልማት ፕሮግራም 18 ሺ 930 ቤቶች፣ በ40/60 ደግሞ 6 ሺ 843 ቤቶች እንዲሁም ተጨማሪ 18 ስቱዲዮ ቤቶች በድምሩ 25 ሺ 791 ቤቶችን እጣ የማውጣት መርሃ ግብር በማካሄዱ የሚዘነጋ አይደለም።

ውል የመዋዋያ ቦታው መገናኛ በሚገኝው የቦሌ ክፍለ ከተማ ቅጥር ግቢ የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ውስጥ መሆኑ ተገልጿል።

20/80 እና 40/60 ውል ፦

የቤት እድለኞች ውል ለመዋዋል ሲመጡ ማሟላት የሚጠበቅባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ምንድናቸው ?

– እጣው የደረሰው ግለሰብ ውል ለመፈፀም በአካል መቅረብ፤

– በውጭ የሚኖሩ ጉዳያቸውን በውክልና ለማስጨረስ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ (አውታንቲኬት) ሆኖ የመጣ ውክልና ማቅረብ፤

– የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

– የጋብቻ የምስክር ወረቀት ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

– ያላገባ/ች ከሆነ/ች 6 ወር ያላለፈው የምስክር ወረቀት፤

– ያገባ/ች ከሆነ/ች የትዳር አጋር የታደሰ መታወቂያ ዋና እና ፎቶ 2 ኮፒ፤

– የምዝገባ ማረጋገጫ (print out) ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤

– የምዝገባ የምስክር ወረቀት ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤

– የባንክ ምዝገባ ማረጋገጫ ከተመዘገቡበት ባንክ የሚቀርብ ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤

– የባንክ የቁጠባ ደብተር ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ (ፎቶ ባለው በኩል)፤

– የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

– ቅጽ -09 (ከወረዳ ተሞልቶ ታሽጎ የሚላክ) ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤

– የጠፋ ሰነድ ካለ የፖሊስ ማስረጃ ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤

– 4×4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ 4፤

– ፍቺ ካለ በፍ/ቤት የፀደቀ ፍቺ ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

– የንብረት ክፍፍል ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

– ባለ ዕድለኛው በሞት ከተለየ የውርስ አጣሪ ሪፖርት ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

– የወራሽነት ማስረጃ ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ ባለ እድለኛው ወይም ወኪሉ ይዞ መቅረብ አለባቸው።

የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያሟላ የሚመጣ ማንኛውም ባለጉዳይ እንደማይስተናገድ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በጥብቅ አሳስቧል።

በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያዊ ከላይ የተጠቀሱትን ማሟላት የግድ ሆኖ ፦

• የታደሰ ፓስፖርት ወይም ቢጫ ካርድ (yellow card) የታደሰ፤

• በውክልና ከሆነ የውክልና ወረቀቱ በጀርባው በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህተም የተረጋገጠ እና የተወካይ የታደሰ መታወቂያ ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል ተብሏል።

ባለዕድለኞች / ወኪላቸው በ60 የስራ ቀናት ውስጥ ካልተዋዋሉ ምን ይፈጠራል ?

ባለእድለኞች ወይም ወኪላቸው ምዝገባ ከተጀመረበት ቀን አንስቶ ባሉት 60 የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርበው ካልተዋዋሉ ቤቱን እንዳልፈለጉት ተቆጥሮ ተመላሽ እንደሚደረግ የከተማው ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአጽንኦት አሳስቧል።

  • ______________
    በገጻችን የምናቀርባቸውን መረጃዎች በአማራጭነት በቴሌግራም ቻናላችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
    👇👇👇👇👇
    t.me/condoaddis
    እንዲሁም፦
    ፌስቡክ:- fb.me/condoadis
Please follow and like us:
Pin Share

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »
RSS
Follow by Email
Scroll to Top