ለማህበር ቤት ግንባታ በተጓደሉት ምትክ የተተኩ እና የተጠባባቂዎች ስም ዝርዝር ተለቀቀ።
በማህበር ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት ተመዝግበው በነበሩ ነገር ግን በእጣ እና በተለያዩ ምክንያቶች የተጓደሉ ተመዝጋቢዎችን የማሟላት እና ተጠባባቂዎችን የመለየት ሥራ በቅርቡ መሰራቱ ይታወሳል።
በዚህም መሰረት በሁለቱም ዲዛይኖች ማለትም በG+9 እና በG+13 በተጓደሉ ምትክ የተተኩ እንዲሁም ወደፊትም በተለያዩ ምክንያቶች የሚለቁ ካሉ በሚል የተጠባባቂዎችን ስም ዝርዝር መመልከት የሚችሉ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ያሳውቃል።